8.1 – አምባገነንን ለማውደም የትግል ሥራ ክፍፍል

August 1st, 2012

This is Ethiopian Review Policy Research Center’s series on From Dictatorship to Democracy extracted from books published by Albert Einstein Institution.

Be inspired! Be coordinated! And take action!

በሀገር ውስጥ ያለው ሕዝብ በከተማ፥ በዱር በገደል በአካል ሲታገል፥ በውጪ ሀገር ያለው የድዮስጶራው ኢትዮጵያዊ ሕዝብ ተደራጅቶ ትግሉን ባለው ትልቅ አቅም ሁሉ ለመደገፍ ፈጥኖ መነሣት አለበት። አቅሙ ለትግሉ በጥቂት ቀናት በሚሊዮን የሚቈጠር ዶላር የሚሰበስብና በምድር ከጽንፍ እስከ ጽንፍ፥ በሰማይ እስከ ራማ የሚደርስ ድምፅ ማሰማት የሚችል በሚሊዮን የሚቈጠር ሕዝብ አቅም ነው። አቅማችንን እናውቃለን፤ ከጓዳ ከትተን እንዲዝግ አናደርገውም፤ ተካትተን ለሕዝባችን ጥቅም እናውለዋለን። ትግሉ ወንድ፥ ሴት፣ ወጣት፥ ሺማግሌ ሳይል የኢትዮጵያውያን ሁሉ ቢሆንም፥ ፊት አውራሪው ዛሬም እንደቀድሞው ወጣቱ እንደሆነ ታሪክና በዚህ ሰሞን በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው ትግል ሕያው ምስክር ናቸው። “ለእናት ኢትዮጵያ ያልሆነ ወጣትነት ለማን ሊሆን ነው? ጎሰኛው ቡድን እናት ሀገርን ታይቶ ከማይታወቅ ሥቃይ ላይ ሲጥላት ያልደረሰላት ወጣትነት ለመቼ ሊደርስላት ነው?” ብሎ እንደሚነሣ ታሪክን ጠቅሰን እናምናለን።—
ትግሉም በአንድነት ተካትቶ እንዳይካሄድ፥ የጎሳው ቡድን የማያደርገው ነገር እንደሌለ አስቀድመን እናውቃለን።
ሕዝቡ ግን ወንድ፥ ሴት፣ ልጅ፥ ሽማግሌ፣ እስላም፥ ክርስቲያን፥ ሃይማኖት አልባ ሳይል፥ የጭቆናው ቀምበር መሮታል፤ ከሃያ ዓመት በላይ መሸከም አልቻለም። የማይለወጥ አቋሙን በምርጫ 97 ተካቶ ባደረገው ድል አሳይቷል። ቅድስቷን ምድር ከጎሰኝነት ርኩስ አገዛዝ ሳያጸዳ ለዓይኑ እንቅልፍ አይሰጥም። ሊታገል የተነሣው፥ የጥንቷ ኢትዮጵያ እንድትታደስ፥ ከራሷ ተርፋ ለሌሎች አርአያና ተስፋ እንድትሆን ነው። በመካተት ሊታገል የተነሣው፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ የፈለገውን ዓይነት መንግሥት ለማቋቋም ዕድል እንዲያገኝ ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕይወት እንድትጥመው በነፃነት፥ በጤና ሠርቶ አትርፎ እንዲኖር ነው፤ ቊጥራቸው ከፍ ያለ አባላት ያላቸው ነገዶች ቊጥራቸው ዝቅ ያለ አባላት ያላቸውን ነገዶች የባህል ጭቆና ሳያመጡባቸው ባህላቸውን እያዳበሩ በሰላም እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፤ ቊጥራቸው ዝቅ ያለ አባላት ያሉት ቡድን ቊጥሩ ከፍ ያለውን ሰፊ ሕዝብ በኢኮኖሚ የማይጨቁንበትን አዲስ ሥርዓት ሕዝቡ እንዲያቋቁም መብቱን ለማስከበር ነው።
እምነታችን በነፃነት አምላክና በአቅማችን ነው።
……..ፕሮ ጌታቸው ኃይሌ

For complete list of the methods of Strategic Popular Mass Uprising actions refer Sharp’s From Dictatorship to Democracy.
To view an illustration of its application Click…Spreading Responsibility to Struggle Against Tyrants